የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU


Channel's geo and language: India, Amharic
Category: Politics


Similar channels

Channel's geo and language
India, Amharic
Category
Politics
Statistics
Posts filter








Forward from: FDRE ATTORNEY GENERAL/ EXTERNAL
የፍትህ ሚኒስቴር ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በመተባበር ‹‹ንቃተ ህግ›› በሚል ርዕስ ዘወትር ሰኞ ከቀኑ 5:30-6:00 ሰአት በፋና ሬድዮ 98.1 ኤፍ ኤም የሚያቀርበውን ፕሮግራም ትከታተሉ ዘንድ ተጋብዛችኋል። https://www.youtube.com/watch?v=lKBI8exnZtU






የአቶ ሙሉጌታ ከበደ አጭር የህይወት ታሪክ

አቶ ሙሉጌታ ከበደ ከአባታቸው ከአቶ ከበደ ተሰማና ከእናታቸው  ከወ/ሮ ወርቅየ ከበደ ግንቦት 19 ቀን 1982 ዓ.ም በደሴ ከተማ ተወለደ።የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ካቤ አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደሴ ቅዳሜ ገበያና ካቶሊክ ትምህርት ቤቶች የመሠናዶ ትምህርቱን በመምህር አካለ ወልድ ትምህርት ቤት ተምሮ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግራውን በወሎ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዲግሪውን በቢዝነስ ሎው ተምሮ በ2013 ዓ.ም የተመረቀ ሲሆን  በስራ ህይወቱ ከአብክመ ፍትህ ባለሙያዎች የህግ ምርምር ኢንስቲትውት የቅድመ ስራ ስልጠና ወስዶ በማጠናቀቅ ሰኔ 22/2008 ዓ.ም በደላንታ ወረዳ ፍርድ ቤት በረዳት ዳኝነት ጀምሮ በዚያው ፍርድ ቤት በዳኝነት ፣ በስራ ሂደት አስተባባሪነትና በሰብሳቢ ዳኝነት ከአምስት አመት በላይ ያገለገለ ሲሆን ከነሐሴ 16/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ህይወቱ እስካለፈበት ጊዜ ድረስ የደሴ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆኖ አገልግሏል።
አቶ ሙሉጌታ ከባለቤታቸው ወ/ሮ ሀያት አልታሰብ ሁለት ልጆችን አፍርተዋል።
ሙሉጌታ በስራው ታታሪ ፣ ከሰዎች ጋር በቀላሉ መግባባት የሚችል፣ ሠው አክባሪና በተመደበበት የኃላፊነት ቦታዎች ሁሉ ብቁ የመምራት አቅም ያለው መሆኑን ያስመሰከረ አርቆ አሳቢና ብዙ ህልሞች የነበሩት ወጣት ነበር።
የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ እና የምድብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች፣ በተዋረድ የሚገኙ የዞን ፍትሕ መምሪያዎች፣የወረዳ እና ንዑስ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤቶች የምንሰራ ዐቃቤያነ ሕግና የአስተዳደር ሠራተኞች በአቶ ሙሉጌታ ከበደ ሞት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቹ፣ለጓደኞቹ ፣ለስራ ባልደረቦቹና ለወዳጆቹ ሁሉ መፅናናትን እንመኛለን።

የአብክመ ፍትሕ ቢሮ




በ2016 በጀት አመት ከ79 ሽህ በላይ መዛግብት እልባት አግኝተዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት

የዐቃቢያን ህግ ተከራክሮ አጥፊዎችን የማስቀጣት አቅም ከ92 በመቶ በላይ ማደጉን የደቡብ ወሎ ዞን ፍትህ መምሪያ አስታውቋል።

ደሴ፣ ጥቅምት 1/2017 ዓ.ም
የ2017 ዓ.ም መደበኛ የዳኝነት አገልግሎት አጀማመር መርሃ ግብር የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የደቡብ ወሎ ዞን ፍትህ መምሪያ ከአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደሴ ምድብ ችሎት ጋር በጋራ በደሴ ከተማ አካሂደዋል።

የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተወካይ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ትዕግስት ዳኛቸው በ2016 ዓ.ም ከቀረቡት ከ82 ሽህ በላይ መዛግብት ከ79 ሽህ በላይ ለሚሆኑት እልባት ተሰጥቷል ብለዋል።

ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች በቴክኖሎጂ የታገዘ ድጋፍ እንደተደረገላቸውም የተገለጸ ሲሆን የውሳኔ ጥራትም እንደተሻሻለ ተመላክቷል።

በ2017 ዓ.ም የዳኝነት አገልግሎቱን በጥራትና በቅልጥፍና ለማሻሻል መታሰቡንም ነግረውናል። ባለፉት ሁለት ወራት የዳኝነት አገልግሎቱ በከፊል ሲሰጥ እንደነበር ያነሱት ወ/ሮ ትዕግስት ከጥቅምት 1/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ የዳኝነት አገልግሎቱ የጀመረ መሆኑን አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል በወንጀል ፍትህ አስተዳደር ከ3 ሽህ 800 በላይ መዛግብት ቀርበው 99 በመቶ የሚሆነውን መርምሮ በማጥራት መወሰኑን የጠቆሙት የደቡብ ወሎ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብርሃም ሞላ ናቸው።

በችሎት ክስ በሚቀርብባቸው ጉዳዮች ተከራክሮ በማሸነፍ አጥፊዎችን የማስቀጣት አቅም ከ92 በመቶ በላይ ማደጉ ተብራርቷል።

ከ1ሽህ 600 በላይ መዛግብት በፍታብሄር ቀርቦ ሙሉ በሙሉ መርምሮ መወሰን እንደተቻለ መምሪያ ኃላፊው አብራርተዋል። በዚህም በከሳሽነት ሙሉ በሙሉ በተከሳሽነት ደግሞ 89 በመቶ በላይ ተከራክሮ የማሸነፍ አቅም ማደጉን አቶ አብርሃም ዘርዝረዋል።
ይህም በመሆኑ መንግስት ተከሶበት በነበረው ዐቃቢያን ህግ ተከራክረው በማሸነፋቸው 180 ሚሊዮን ብር ማዳን ተችሏል። 540 ሄክታር መሬት ወደ መንግስት መሬት ባንክ እንዲገባ መደረጉንም አክለዋል አቶ አብርሃም። በውልና ማስረጃ የተቀላጠፈ አገልግሎት 541 ሚሊዮን ብር ገቢ እንደተገኘም ገልጸዋል።

በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደሴ ቋሚ ምድብ ችሎት አስተባባሪ ወ/ሮ ደብረወርቅ ገብሬ እንዳሉት ደግሞ ሪፎርሙ ተግባራዊ በመደረጉ ቀልጣፋ የዳኝነት አገልግሎትን ለኅብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ተችሏል። በክልሉ በተለያዩ ዞኖች ደረጃውን የጠበቀ ሕንጻ በመገንባት በቴክኖሎጅ የታገዘ አገልግሎት እንደተሰጠም ጠቁመዋል። በ2017 ዓ.ም አገልግሎቱን የበለጠ በማዘመንና በማቀላጠፍ የማኅበረሰቡን እርካታ ለመፍጠር እንደሚሠራም አረጋግጠዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ




የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደሴ ቋሚ ምድብ ችሎትና የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2017 ዓ.ም የችሎት ስራዎች የማስጀመሪያ መድረክ በፍርድ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ።
የቋሚ ምድብ ችሎት አስተባባሪ ወ/ሮ ደብረወርቅ ገ/ህይወት ፣ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ተወካይ ፕሬዝዳንት ወሮ ትዕግስት ዳኛቸውን ጨምሮ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ደሴ ምድብ አስተባባሪ አቶ ድልባንተ ደባሹና የፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብርሀም ሞላ በመድረኩ ለተገኙ የምድብ ችሎቱና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችና ሰራተኞች መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የሀላፊ ተወካዮች የደሴ ከተማና የደሴ ዙርያ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶችና የዋና የስራ ሂደት አስተባባሪዎች ተገኝተዋል። መድረኩ በዝህብ ግንኙነት ስራ ሂደት " አዎ ዳኛ ስትሆን " በሚል ርዕሰ በቀረበ ግጥምና በቡና ስነስርአት ታጅቦ በቀጣይ በዞኑ ካሉ ሁሉም የፍትህ ተቋማት ጋር ተባብሮ በመስራት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሊሰሩ በሚገባቸው ስራዎች ላይ ወይይት ተደርጐ በሁሉም ዳኞች ፣ ሰራተኞችና የጉባኤ ተሿሚዎች ቃል የመግባት ስነስርአት ተጠናቋል።የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዝብግንኙነት




ለዳኝነት ሥርዓቱ መሻሻል የጠበቆች ሚና ከፍተኛ መኾኑ ተመላከተ።

ባሕር ዳር: መስከረም 28/2017 ዓ.ም የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የክልሉን የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻል በሚቻልበት መንገድ ላይ በክልሉ ከሚገኙ ጠበቆች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሙሉዓለም ቢያዝን የዳኝነት ሥርዓቱን ፈጣን ቀልጣፋ እና ወጭ ቆጣቢ ለማድረግ እና ነጻ የዳኝነት ሥርዓት ለመገንባት የሦስት ዓመት ዕቅድ ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን ገልጸዋል።

የፍርድ ቤቶች ማሻሻያ የመጨረሻ ግቡ ለኅብረተሰቡ ተደራሽ፣ ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ የኾነ የዳኝነት ሥርዓት መገንባት ብሎም የሕዝብ አመኔታ ያለው ስመ ጥር ፍርድ ቤት መፍጠር ነውም ብለዋል።

ምክትል ፕሬዚዳንቱ ለዚህም መድረኮችን በመፍጠር እና በመወያየት መግባባት ላይ እየተደረሰ እንደኾነም አስረድተዋል።

ጠበቆች ለዳኝነት ሥርዓቱ መጎልበት ካላቸው ሚና አኳያ ምን እየሠሩ፣ ምን ችግር እያጋጠማቸው እና ለወደፊት መፍትሄ በሚኾኑ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት እና ለመግባባት መድረኩ መፈጠሩንም ገልጸዋል።

የመወያያ ሃሳብ ያቀረቡት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት አማካሪ ረዳት ፕሮፌሰር ወርቁ ያዜ በኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት ጠበቆች ጉልህ ሚና ያላቸው መኾኑን ገልጸዋል።

ይሁን እንጅ በዳኝነት፣ በዐቃቢ ሕግ እና በጠበቆች ላይ የሚነሱ የሥነ ምግባር ቅሬታዎች መኖራቸውን አንስተዋል።

በሕግ ፊት ሁሉም እኩል መኾኑን ለማረጋገጥ የጠበቆችን አይተኬነት ጠቅሰዋል። የዳኝነት አካል የተሳሳተ ትዕዛዝ እና ውሳኔ እንዳይወስን በመከላከል በኩልም ያላቸው ድርሻ ከፍ ያለ ስለመኾኑ ጠቅሰዋል፡፡

በጠበቆች ላይ የሚታዩ የሥነ ምግባር ጉድለቶች የፍትሕ መጓደል ብቻ ሳይኾን ማኅበራዊ ችግር እየፈጠሩ መኾኑን ገልጸዋል።

ለዚህም መፍትሄ እንዲኾን በፍርድ ቤት እና በዳኞች ሊወሰዱ የሚገባቸው ማስተካከያዎች ለተሳታፊዎቹ ቀርበዋል፡፡

አሚኮ



14 last posts shown.