ደሴ ጥላሁን (ዶ/ር) የአማራ ክልል የፍትሕ እና ሕግ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ
የካቲት 27/2017፦የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ፤ ደሴ ጥላሁን(ዶ/ር)ን የክልሉ የፍትሕ እና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ አበራን ደግሞ ምክትል ዳይሬክተር አድርገው ሾመዋል፡፡
ተሿሚዎቹ ያላቸውን የካበተ ልምድ፣ ክህሎት እና ዕውቀት በመጠቀም የክልሉን የፍትሕ አሥተዳደር ሥርዓት ለማዘመን እና ለማሻሻል ለሚደረገው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ የበኩላቸውን አሻራ ያሳርፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል፡፡
ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጠሪ የሆነውን የአማራ ክልል የፍትሕ እና ሕግ ኢንስቲትዩት ፤ የክልሉ ምክር ቤት ከየካቲት 4 እስከ 7 /2017 ዓ.ም ባካሄደው 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት፣ 9ኛ መደበኛ ጉባኤ እንደገና ማቋቋሙ ይታወቃል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ብቃት፣ ክህሎት እና መልካም ሥነ ምግባር የተላበሱ የዳኝነት እና የፍትሕ ባለሙያዎችን የማፍራት ተልዕኮውን በአግባቡ እንዲወጣ በማድረግ፣በክልሉ የፍትሕ አሥተዳደር ሥርዓት ላይ ጉልህ መሻሻል እንደሚያመጣ ተገልጿል።
https://www.facebook.com/share/19t88Axp2q/